የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች ለመዲናዋ ልማት በትጋትና በቁርጠኝነት ያገለገሉ አመራሮችን አመሰገኑ

By tigist gizachew

October 06, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት ዓመታት ለአዲስ አበባ ከተማ ሁለንተናዊ ልማት በትጋትና በቁርጠኝነት ላገለገሉ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ባለፉት ዓመታት ለአዲስ አበባ በትጋትና በቁርጠኝነት ያገለገሉ አመራሮች ወደ ሌላ አዲስ የኃላፊነት ቦታ በመመደባቸው በክብር ሸኝተናል ብለዋል።

በአዲስ አበባ የነበረን የጋራ አመራር፣ የጋራ ጥረትና የጋራ ዐሻራችን ሁሌም ይኖራል ያሉት ከንቲባ አዳነች ÷ ለሰጡት አገልግሎትና ለከተማዋ ልማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

አመራሮቹ በሄዱበት ሁሉ የአዲስ አበባ ከተማን ልምድና ተሞክሮ በማስፋት የበለጠ ስኬትና ውጤት እንዲያስመዘግቡም ተመኝተዋል፡፡

በሌላ በኩል ወደ አዲስ አበባ አዲስ ኃላፊነት ተረክበው ለመጡ አመራሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አዲሱን የኃላፊነት ምዕራፍ በትጋት፣ በአንድነትና በጋራ አመራር፣ ለመዲናዋ ሕዝብ የበለጠ የሚታይ ለውጥና የላቀ ውጤት የምናስመዘግብበት ይሁን ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡