አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡለትን የሚኒስትሮች ሹመት አጽድቋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በመደበኛ ስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቢኔያቸውን እጩ አባላት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 2. አቶ አዲሱ አረጋ – የግብርና ሚኒስትር
3. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) – የገንዘብ ሚኒስትር 4. አቶ መሃመድ እድሪስ – የመከላከያ ሚኒስትር
5. ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) – የትምህርት ሚኒስትር 6. ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ – የፍትሕ ሚኒስትር
7. ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ – የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር 8. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
9. ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) – የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር 10. መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) – የጤና ሚኒስትር
11. አቶ አወሉ አብዲ- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር 12. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ – የገቢዎች ሚኒስትር
13. አቶ በረከት ፍስሃጽዮን – የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር 14. ሰላማዊት ካሳ- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
15. ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ – የማዕድን ሚኒስትር 16. አቶ ሳዳት ነሻ – የሎጂስቲክስ ሚኒስትር
17. ወ/ሮ ሻዊት ሻንካ – የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር 18. አቶ ሙሳ አደም – የሰላም ሚኒስትር
19. ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ – የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር 20. መሃመድ አብዱራሃማን (ኢ/ር) – የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
21. ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) – የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር 22. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) – የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው በእጩነት ቀርበዋል፡፡
ምክር ቤቱም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረቡለትን የሚኒስትሮች ሹመት አጽድቋል፡፡
የአዲሱ የመደመር መንግሥት ተሿሚ ሚኒስትሮችም በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
#የመደመርመንግሥት
በመላኩ ገድፍ