የሀገር ውስጥ ዜና

የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

By sosina alemayehu

October 08, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ አዲስ አበባ  ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በጉብኝቱ በኢትዮጵያ እና በሕንድ መካከል ያለውን ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ውይይቶች የሚያደርጉ ይሆናል።