የሀገር ውስጥ ዜና

በአእምሮና በአካል ብቁ የሆነ ትውልድ በመደመር ተምሳሌት ከተማ እንገነባለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

By Melaku Gedif

October 11, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአእምሮና በአካል ብቁ፤ በአስተሳሰብ ንቁ የሆነ ትውልድ በመደመር ተምሳሌት ከተማ እንገነባለን አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ ዛሬ ማለዳ ከከተማችን ነዋሪዎችና አመራሮች ጋር ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አካሂደናል ብለዋል።

በዚህ ወቅትም በአእምሮና በአካል ብቁ እንዲሁም በአስተሳሰብ ንቁ የሆነ ትውልድ በመደመር ተምሳሌት ከተማ እንገነባለን ሲሉ ተናግረዋል።