የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ

By Mikias Ayele

October 11, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ዛሬ ጀምሯል።

የአየር መንገዱ አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ መቐለ ከተማ አርፏል።

ትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በረራ መጀመሩን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች በአሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ደስታቸውን እየገለጹ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ቀን ወደ መቐለ በረራ ማድረግ እንደሚጀምር ማስታወቁ ይታወሳል።