አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የሚያስደንቅ መልክዓ ምድር የታደለችና በጥንታዊ ሥልጣኔ የገነነ ትልቅ ሕዝብ መገኛ ናት፡፡
ሀገሪቱ በባህል እና ቅርስ ሃብት የበለጸገች ብትሆንም፣ ይህንን ፀጋዋን በመጠቀም የሚገባትን ጥቅም ማግኘት ላይ ግን ችላ ብላ ቆይታለች።
ዛሬ ግን የ’መደመር’ ፍልስፍና የጋራ አቅምና ችሎታዎችን በማቀናጀት አመርቂ ውጤቶችን የማስመዝገብ ታላቅ ርዕይ ላይ የተመሠረተ እንደመሆኑ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት እና ተጨባጭ ለውጥ እየተመዘገበ ይገኛል፡፡
በመደመር እሳቤ ከተቃኙ እና ከተነቃቁ ዘርፎች አንዱ የሆነው ቱሪዝምም ወደ ሀገሪቱ ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶነት ከፍ ብሎ እየተሰራበት ነው፡፡
በቱሪዝም ዘርፍ የመደመር ፍልስፍና የመስህብ ስፍራ እና አገልግሎት ማዘመንን፣ የአካባቢ ጥበቃን፣ ባህልና ቅርስን ማበልጸግ እንዲሁም መጠበቅን የመሰረተ ልማት ማስፋፋትን እና ከመሳሰሉት ጋር ያገናኛል።
እነዚህን ዘርፎች የመደመር ማዕቀፍ የመንግሥት ሃብትን፣ የማህበረሰብ ተሳትፎን እና ራዕይ ያለው አፈጻጸምን በማቀናጀት ተገቢው ትኩረት ተነፍጓቸው የቆዩ የመስህብ ስፍራዎችን ዘላቂ ወደሆኑ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ለውጧል።
መንግሥት ቱሪዝምን እንደ ልማት ምሰሶ በመለየት ንቁ እሴት የመፍጠር አካሄድን የተከተለ ሲሆን÷ ይህ መንገድ ቅርሶች እና የተፈጥሮ ሀብቶች ሀገሪቱ የምትገባውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትርፍ ለማግኘት ዘመናዊ መሠረተ ልማት፣ የተቋማት ቅንጅት እና የዲጂታል ትስስር እንደሚያስፈልጋቸው ተገንዝቧል።
እንደ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ያሉ ፕሮጀክቶች ብሔራዊ የሀብት እና አቅም ድምር አስደናቂ ታሪክ መስራት እንደሚችል በተግባር ያሳያሉ።
የሕዝብ እና የግል አቅሞችን በማቀናጀት እንደ ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ ያሉ መዳረሻዎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሪዞርቶች እና የኢኮ-ቱሪዝም ማዕከሎች እንዲሆኑ ተደርገው በመገንባታቸው ከዘርፉ የሚገኝ የኢኮኖሚ ዕድገት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አስችለዋል።
በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ የተከናወኑ አጠቃላይ የከተማ ማዘመን ስራዎች ደህንነትን፣ ተደራሽነትን እና የጎብኝዎችን ፍሰት በማሻሻል ከተማዋን ለኑሮ ምቹ እንዲሁም ለኮንፍረንስ ቱሪዝም ተመራጭ አድርገዋታል።
ይህንን ተከትሎ የተገኙ አንጸባራቂ ውጤቶች የመደመርን መንገድ ስኬታማነት የሚያረጋግጡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ናቸው፡፡
አዳዲሶቹ ቱሪስት መዳረሻዎች ሥራ ከጀመሩበት ጊዜ አንሥቶ በአጭር ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት የውጭ ምንዛሪ ገቢን በእጅጉ ጨምረዋል። በዘርፉ የተደረጉ ኢንቨስትመንቶች ማህበረሰቡ የሚዝናናባቸው ስፍራዎች ከመሆናቸውም በላይ የሀገሪቱ ኢኮኖሚው የጀርባ አጥንት መሆናቸውን አሳይተዋል።
የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችን ጥበብ ገላጭ በመሆን በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር በተለይም ወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚ አድርጓል።
የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ለውጥ እንደሚያሳየው እንዲት በማደግ ላይ ያለች ሀገር ጠባቂነትን እና ጥገኝነትን በማስወገድ በአንጻሩ ማሕበረሰብን በመደመር ፍልስፍና በማስተባበር አዕምሯዊና ተፈጥሯዊ አቅሟን በጋራ ርዕይ ስታሰባስብ ታሪክ መስራት ትችላለች፡፡
በመደመር መንግሥት መሪነት ኢትዮጵያ በዘላቂ እድገት ላይ የተመሰረተች ዓለም አቀፍ መዳረሻነቷን አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡
#ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
በምህረት ደምሴ