የሀገር ውስጥ ዜና

የሠንደቅ ዓላማ ቀን ኢትዮጵያዊ ማንነትን በጋራ የምናጎለብትበት ታላቅ ብሔራዊ ዕለት ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ

By Melaku Gedif

October 12, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሠንደቅ ዓላማ ቀን ሕብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊ ማንነትን በጋራ የምናጎለብትበት ታላቅ ብሔራዊ ዕለት ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ።

“ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሃሳብ መከበር የጀመረውን የሠንደቅ ዓላማ ቀን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አስጀምረዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሠንደቅ ዓላማ ቀን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር፣ ክብርና ቃል ኪዳን በልቡ የሚያድስበት ነው ብለዋል።

እንዲሁም ሕብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊ ማንነትን በጋራ የምናጎለብትበት ታላቅ ብሔራዊ ዕለት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ አሕመድ ሺዴ፣ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት እና የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ፍቃዱ ተሰማን ጨምሮ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ