የሀገር ውስጥ ዜና

ሰንደቅ ዓላማችን የኢትዮጵያን አኩሪ ታሪኮች፣ ድሎች፣ ገድሎችና ማንነት የሚወክል ነው – ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር)

By sosina alemayehu

October 12, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰንደቅ ዓላማችን የኢትዮጵያን አኩሪ ታሪኮች፣ ድሎች፣ ገድሎችና ማንነት የሚወክል ነው አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)።

19ኛው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት ተከብሯል።

ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ፥ ሰንደቅ ዓላማን ከፍ አድርጎ ለማውለብለብ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አስተዋፅኦ እና አበርክቶ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን የሃገራቸውን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር በአግባቡ ሲያስጠብቁ፣ ሃገራቸውን ሲያሳድጉና ሲያበለጽጉ እንዲሁም ታሪካቸውን ሲያስቀጥሉ በሰንደቅ ዓላማቸው ላይ ያላቸው ኩራት የሚጎላ መሆኑን አብራርተዋል።

ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የሃገርን ሉአላዊነትና ባንዲራን ለማስከበር በየድንበሩ መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉ ጀግኖችን ታሳቢ በማድረግ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተሰማራበት የስራ መስክ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ አሳስበዋል።

#ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ