የሀገር ውስጥ ዜና

የነፃነታችንና የሉዓላዊነታችን ምስክር የሆነውን ሠንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገን በማክበራችን ኩራት ይሰማናል

By tigist gizachew

October 12, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የነፃነታችንና የሉዓላዊነታችን ምስክር የሆነውን ሠንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገን በማክበራችን ኩራት ይሰማናል አሉ ለፋና ዲጂታል አስተያየታቸውን የሰጡ የማህበረሰብ ክፍሎች፡፡

19ኛው የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።

ሠንደቅ ዓላማችን ከዓድዋ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የነፃነታችንና የሉዓላዊነታችን ምስክር ነው ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ፡፡

በሀገር ውስጥና በውጭ በየትኛውም ዘርፍ የምንገኝ ብንሆንም እንኳን ለኢትዮጵያ ከፍታ በጋራ መቆም ይገባናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሠንደቅ ዓላማ የሀገርን ሀሳባዊ ትዕምርትና የታሪክ መስታወት የሚያንፀባርቅ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ የአፍሪካ ነፃነት ፈር ቀዳጅ ዓርማ እንደሆነም አንስተዋል፡፡

ሠንደቅ ዓላማችን የጋራ ታሪካችን፣ የሉዓላዊነታችን ምልክትና የአንድነታችን መሠረት ነው ብለዋል።

በልዩነታችን ውስጥ አንድነታችንን አጠናክረን፣ ለሰላምና ለጋራ ብልጽግና በአንድነት መቆም ሀገራችንን ወደ ከፍታ ለመውሰድ መስራት አለብን ሲሉ አክለዋል፡፡

በመሆኑም ዛሬ ሠንደቃችንን ከፍ አድርገን ስንሰቅል ለነገዋ ለበለጸገችና ሰላሟ ለተጠበቀ ኢትዮጵያ አዲስ ተስፋ እንሰንቃለን ነው ያሉት፡፡

#ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በእመቤት ሲሳይ