የሀገር ውስጥ ዜና

የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥን የማስፋፋት ሥራ እየተካሄደ ነው – አቶ ሙስጠፌ መሀመድ

By betelhem girma

October 12, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥን የማስፋፋት ሥራ እየተካሄደ ነው አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በክልሉ ሶስተኛ የሆነውን ጅግጅጋ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡

በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት÷ መሶብ የአንድ ማዕከል ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎት ለመስጠት እያስቻለ ነው።

በዚህም በወረዳዎችና በከተማ አስተዳድሮች ማዕከላቱን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ጊዜና ወጪ ለመቀነስና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ ነው ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።