የሀገር ውስጥ ዜና

የሳዑዲ አልጋ ወራሽ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

By sosina alemayehu

October 13, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሙሐመድ ቢን ሰልማን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሙሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ በመልዕክታቸው፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) ለአዲስ የአምስት ዓመት የሥራ ዘመን በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

አልጋ ወራሹ ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕዝብ ቀጣይነት ያለው እድገትና ብልጽግናን መመኘታቸውን የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ(SPA) ዘግቧል።