የሀገር ውስጥ ዜና

ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመውጣት ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል – ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)

By tigist gizachew

October 14, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመውጣት ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት የውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በምግብ ራስን መቻል ከምግብ ዋስትና በላይ የብሔራዊ ክብራችንና የሉዓላዊነታችን ዋነኛ ምሰሶ ነው፡፡

ለበርካታ አስርት ዓመታት ስር ሰዶ የቆየውን የተረጂነት አስተሳሰብ ለመስበር ሁላችንም በየተሰማራንበት መስክ ወደ ላቀ ምርታማነት መሸጋገር አለብን ብለዋል፡፡

‌‎ክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በርካታ ስትራቴጂካዊ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፤ በተለይም «ለአንድ የሰብዓዊ ድጋፍ ተረጂ አንድ የሥራ መስክ» የሚል አዲስ መርህ ይፋ መደረጉ ተገልጿል።

በዚህም በክልሉ ካሉ 87ሺህ 971 ተረጂዎች እስካሁን 22ሺህ 412 ለሚሆኑት አዲስ የሥራ ዕድል በመፍጠር ራሳቸውን እንዲችሉ መደረጉ ተመላክቷል፡፡

በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች ከተፈናቀሉ 11ሺህ 940 ዜጎች ውስጥ 4ሺህ 759 የሚሆኑትን የመልሶ ማቋቋም ስራ እንደተሰራም ተጠቁሟል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

‎በመለሰ ታደለ