የሀገር ውስጥ ዜና

አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሽግግርና እድገት የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አረጋገጠ

By betelhem girma

October 14, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ለኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሽግግርና እድገት የሚያደርጋውን ድጋፍ በዘላቂነት እንደሚቀጥል አረጋግጧል፡፡

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በታይላንድ ባንኮክ መካሄዱን ቀጥሏል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በዓመታዊው ስብስባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከዓመታዊው ስብስባው ጎን ለጎን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ናይጀል ክላርክ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ናይጀል ክላርክ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳን ለማስቀጠል ያላት ጠንካራ ተነሳሽነት፣ ጥረት እና ጽናት አድንቀዋል።

ሀገሪቱ ያጋጠሟትን ፈተናዎች በሚገባ በመቋቋም ያሳየችውን ቁርጠኝነት ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አይኤምኤፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር እና ለሀገሪቱ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሽግግርና እድገት የሚያደርገውን ዘላቂ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ