የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ዴንማርክ በአየር ንብረት ለውጥ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

By tigist gizachew

October 14, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ዴንማርክ በአየር ንብረት ለውጥ ያላቸውን አጋርነት የበለጠ የሚያጠናክር አዲስ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ በገንዘብ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ሱኔ ክሮግስትሩፕ አማካኝነት ተፈርሟል፡፡

በተደረገው ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ያሏትን ቅድመ አጀንዳዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና ለማሳየት የሚያስችላትን የገንዘብ ድጋፍ ዴንማርክ እንደምታቀርብ ተመላክቷል።

ይህ አዲስ ስምምነት ዴንማርክ ቀደም ሲል ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ሁነቶች ላይ ስታደርግ ለቆየችው ንቁ ተሳትፎ መሰረት ያደረገ ነው፡፡

በተጨማሪም ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ዘላቂ የወደፊት ወዳጅነትና አጋርነት የበለጠ እንደሚያጠናክር ነው የተገለጸው፡፡