አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የ78ኛው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆና ተመረጠች፡፡
77ኛው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዓመታዊ ስብሰባውን በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እያካሄደ ይገኛል፡፡
በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ የ78ኛው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆና ተመርጣለች፡፡
ኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከተለያዩ ሀገራት ተቀብላ በማስተናገድ ላይ መሆኗን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ገልጿል፡፡
በኮሚሽኑ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሊቀመንበርነት መመረጧ ለስደተኞች ጥበቃና እንክብካቤ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ ታሪካዊ እውቅና መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡