የሀገር ውስጥ ዜና

ፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ነገ ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል

By emebet sisay

October 16, 2026

የተወዳጁ ፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ውድድር ነገ ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል፡፡

ሁለት ሳምንታት ወደ ቀሩት የፍጻሜ ውድድር ለመድረስ በሚደረገው ብርቱ ፉክክር 6ቱ ተወዳዳሪዎች በሁለት ዙር ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡በባንዶች የሙዚቃ ምርጫም ይፈተናሉ።

በረከት መስፍን፣ ዳዊት አታላይ፣ አማኑኤል ሙሉሃብት፣ ሃና ተስፋዬ፣ ሃ/ማርያም ተገኑ እና ሃይለኢየሱስ ታደገ የነገ ተወዳዳሪዎች ናቸው፡፡

ወደ ምዕራፉ ፍጻሜ የሚገቡ 4 ተወዳዳሪዎች በቅርቡ ለሚጀመረው 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ።

ፋና ላምሮት ነገ ቅዳሜ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን፣ በፋና ፕላስ እና በዲጂታል አማራጮች በቀጥታ ሥርጭት ወደ እርስዎ ይደርሳል።

በለምለም ዮሀንስ