አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በበጋ የተቀናጀ የግብርና ዘርፎች ምርታማነትን በማሳደግ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ክልላዊ የግብርና ምርቶች ኤግዚቢሽን መርቀው ከፍተዋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የበጋ ስራዎች የንቅናቄ መድረክ አስመልክቶ የተዘጋጀው የግብርና ምርቶች ኤግዚቢሽን አምራቹን እና ሸማቹን ማህበረሰብ በቀጥታ ማገናኘት እንደሚያስችልም ተመላክቷል።
በኤግዚቢሽኑ ከዚህ ቀደም በክልሉ ያልተለመዱ የግብርና ምርቶች ለእይታ በቅተዋል።
በክልሉ በመደመር መንግሥት ምስረታ ማግስት የተዘጋጀው ይህ የግብርና ምርቶች ኤግዚቢሽን አርሶ አደሩ በዘመናዊ ግብርና ላይ ያለውን ግንዛቤ የሚያሳድግበት መሆኑም ተጠቁሟል።
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
በጌታቸው ሙለታ