አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በኤአይ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ አቅም አላት አለ የዓለም ጤና ድርጅት።
ከዓለም ጤና ድርጅት የመጡ ልዑካን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተው፣ በጤናው ዘርፍ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አብሮ መሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከኢንስቲትዩቱ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት ኢንስቲትዩቱ በተፈጥሮ ቋንቋ ቅንብር (NLP)፣ በማሽን ቋንቋ እና በንግግር ማወቂያ ቴክኖሎጂዎች ያከናወናቸው ሥራዎች ለጤናው ዘርፍ ሰፊ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተገልጿል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) የጤና አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ ለማድረግ የተዘጋጁ የኤአይ መፍትሔዎችን ያስተዋወቁ ሲሆን፣ ቴክኖሎጂው በአንደኛ ደረጃ የጤና ተቋማት ውስጥ ሥራ ላይ በሚውልበትና የሕክምና ባለሙያዎችን አቅም በሚያሳድግበት ሁኔታ ላይ መከረዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ልዑካን በበኩላቸው ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመሥራትና አጋርነትን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው አረጋግጠዋል።
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ