አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያና ኬንያ የረጅም ጊዜ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያላቸው ጎረቤት ሀገራት ናቸው፡፡
የኢትዮጵያና የኬንያ ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ከታሪካዊው የድንበር ስምምነት ጀምሮ እስከ አሁን በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ በታሪካዊ ወዳጅነትና በጋራ ተጠቃሚነት ማዕቀፍ ውስጥ ከሚጠቀሱ የዲፕሎማሲ ትብብሮች መከካል አንዱ ነው።
የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በየዘመናቱም የመሪዎችና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነታቸው ባልተቋረጠ መልኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስራቸውን ለማሳደግ እና የንግድ ልውውጥን ለማስፋት በየጊዜው እየሠሩ ሲሆን፤ የሁለቱን ሀገራት ዜጎች ማኅበራዊና ባህላዊ ትስስር ማጠናከር ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያና ኬንያ ግንኙነት መጠናከር ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡
የኢትዮጵያና የኬንያ ሁለንተናዊ ግንኙነት በመከባበርና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ብቻ ሳይሆን፤ የአህጉሪቱን ነጻነትና አንድነት ከፍ ለማድረግ ጽኑ መሠረት የጣለ የፓን-አፍሪካኒዝም ህያው ተምሳሌት ነው።
የሁለቱን ሀገራት ግንኙነትና ብሄራዊ ፍላጎት ማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ በኢኮኖሚ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በማህበራዊ እንዲሁም በቀጣናዊ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ሀገራቱ በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከምንጊዜውም በላይ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በጋራ መስራታቸውን አጠናከረው ቀጥለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኬንያ ኤልዶሬት በዛሬው ዕለት በተከበረው የማሹጃ ቀን (የጀግኖች ቀን) ብሔራዊ ክብረ በዓል ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በንግግራቸው ለሀገራቸው ነጻነት ለታገሉና ሉዓላዊነታቸውን ለማስከበር ታላቅ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ያላቸውን ታላቅ ክብር ገልጸዋል።
ጀግኖቹ ላበረከቱት አስተዋጽዖ እና ትተውት ላለፉት አሻራ ላቅ ያለ እውቅና ሰጥተዋል።
የኬንያ የጀግንነት እና የመስዋዕትነት ታሪክ፣ ከሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘናት የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለመከላከል በአንድነት ከቆሙበት ከኢትዮጵያ የዓድዋ ታሪክ ጋር በእጅጉ እንደሚመሳሰል አንስተዋል።
በድንበር አካባቢ የሚገኙ የሁለቱም ሀገራት ዜጎች በባህል፣ በቋንቋ፣ በንግድ፣ በግብርና እና በቱሪዝም መስክ ግንኙነታቸውን ማጠናከር ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡
የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ የግንኙነትና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን በተሻለ መልኩ ለማጠናከርና ለማሳለጥ ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን መዘርጋት ጉልህ ሚና አለው፡፡
በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የቀጣናውን የሰላም ሁኔታ ከማጠናከር አኳያ እንዲሁም አልፎ አልፎ ከሚከሰቱ ድንበር ዘለል ግጭቶች እና መፍትሔዎቻቸው ዙሪያ ትልቅ ሚና ይኖረዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እንዲሁም በጸጥታና ደህንነት ዘርፎች ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡