የሀገር ውስጥ ዜና

ትክክለኛ የመረጃ ትንተና ለዘላቂና አስተማማኝ ልማት ወሳኝ ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ

By tigist gizachew

October 21, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ትክክለኛ የመረጃ ትንተና ለአካታች፣ ዘላቂና አስተማማኝ ልማት ወሳኝ ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፡፡

10ኛው የአፍሪካ ስታትስቲክስ ኮሚሽን መደበኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ፕሬዚዳንት ታዬ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ እድገት በትክክለኛው መንገድ ካልተለካና ካልተመዘገበ የልማት ሂደቱን ማወቅ አይቻልም፡፡

የመረጃ ትንተናን ዘላቂ እና አስተማማኝ ለማድረግ ዳታ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ ትንተናን ትክክለኛ ለማድረግ በተለያዩ ዘርፎች የዲጂታል የአሰራር ስርዓትን መዘርጋቷን አንስተዋል፡፡

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ክላቨር ጋቴቴ በበኩላቸው÷ ዳታን መፍጠርና መጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አንስተው፤ በተለይም የስራ አጥነትን ለመቀነስ እና ድህነትን ለመዋጋት የሰራተኛውንና የወጣቱን አቅም ማወቅ ይገባል ብለዋል።

ክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም፣ ሀሰተኛ መረጃዎችን መከላከል እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ከጂኦስፓሻል መረጃዎች ጋር በማስተሳሰር አስተማማኝ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በስታቲስቲክስ ኤጀንሲዎች ላይ ትክክለኛ በጀት በመመደብ በብቃት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዓለምሰገድ አሳዬ