የሀገር ውስጥ ዜና

በደብረ ማርቆስና እንጅባራ ከተሞች መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

By betelhem girma

October 22, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በደብረ ማርቆስና እንጅባራ ከተሞች መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ሴቶችና ወጣቶች እንዲሁም ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

ሰልፈኞቹ የሠራዊቱን ሕዝባዊነትና ጀግንነት እንዲሁም የሀገር መከታ መሆኑን የሚያሳዩ መፈክሮች፣ የሀገር ብሄራዊ ጥቅምና በተለይም የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን እያስተጋቡ ነው።