አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በመቐለ ከተማ የፊታችን ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሒደት ለመጀመር ዝግጅት ተደርጓል አሉ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሽሻይ አማረ (ዶ/ር)።
ከንቲባው ከመቐለ ከተማ መምህራን እና ከትምህርት ቤት አስተዳደር አካላት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም መምህራንና ወላጆች የትምህርት ሥራው በስኬት እንዲቀጥል የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የትምህርት ሒደቱ እንደገና መጀመሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና በጉዳት ምክንያት የተቋረጠው የትምህርት አገልግሎት እንዲቀጥል የሚያግዝ መሆኑን ከንቲባው ገልጸዋል።
ከንቲባ ሽሻይ አማረ (ዶ/ር) በጉዳት ምክንያት የትምህርት ሥራ የተቋረጠባቸውን የአፄ ዮሐንስ ት/ቤት እንዲሁም አይደር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመጎብኘት ያለበትን ሁኔታ ተመልክተዋል።
በግዛቸው ግርማዬ