አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሥራ ጊዜ ተጠናቅቋል አሉ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ፡፡
መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በ4 ዓመት ከ7 ወራት ጊዜ ውስጥ የተሰጠውን ኃላፊነት በስኬት አጠናቅቋል፡፡
የምክክር ሒደቱም ለዘመናት የዘለቁ አለመግባባቶችን በውይይት መፍታት እንደሚቻል መሰረት የጣለ ነው ብለዋል፡:
በምክክር ሒደቱ የቀረቡ ምክረ-ሃሳቦች ተፈጻሚ የሚሆኑት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገራቸውን ችግር በምክክርና በውይይት ለመፍታት ያደረጉት ጥረት ለሒደቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የምክክር ኮሚሽኑ እስከ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የተፈቀደለትን ኃላፊነት በማጠናቀቁ ከዚህ በኋላ ከተቋሙ የሚሰጡ ሃሰቦችም ሆኑ መግለጫዎች እንደማይኖሩ አስገንዝበዋል፡፡
በምክክር ሒደቱ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት ምስጋና ያቀረቡት ዋና ኮሚሽነሩ÷ በቀጣይ የኮሚሽኑ ተግባር መረጃዎቹን የመሰነድና የዲጂታል ተግባራትን ማከናወን መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በአመለወርቅ መኳንንት