የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል የመንግሥትና ፓርቲ የሩብ ዓመት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ

By Mikias Ayele

October 24, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት እና የፓርቲ  የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተጀምሯል።

በግምገማ መድረኩ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችና የነበሩ ክፍተቶች ላይ ውይይት ይደረጋል።

በተጨማሪም በቀጣይ በሚከናወኑ ሥራዎች ላይ እንዲሁም የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠልና የታዩ ተግዳሮቶችን ለማረም የሚያስችሉ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ተመላክቷል።

በአቤል ነዋይ