የሀገር ውስጥ ዜና

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

October 24, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ኪቱሬ ኪንዲኪ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ 12ኛውና ከፍተኛ የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ የሆነው ጣና ፎረም ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ የኬንያውን ምክትል ፕሬዝዳንት ኪቱሬ ኪንዲኪን በመቀበሌ የተሰማኝን ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል።

ከምክትል ፕሬዚዳንት ኪቱሬ ኪንዲኪ ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያም አጭር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ነው ያሉት።