አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የታጠቀ ኃይል ታሪክ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው አሉ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ወታደራዊ አማካሪ እና የመከላከያ የተኩስ አመራር ኃላፊ ጄኔራል ዓለምሸት ደግፌ፡፡
119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን “የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት እየተከበረ ነው።
ጄነራል ዓለምእሸት ደግፌ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ህዝባችን ህልውናውን ያቆየው አንድነቱን እየጠበቀ ከውጪ የሚነሱ ኃይሎችን ተባብሮ በማድቀቁ ነው፡፡
119ኛ የሠራዊት ቀን ስናከብር የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ መሰረት የተጣለበትን ዕለት ለመጥቀስ እንጂ፤ ይህ ቁጥር እንደ ሀገር ይመጥነናል ብለን እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል ብለዋል፡፡
ሠራዊቱ ኢትዮጵያን ለማቆየት ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለ ኃይል መሆኑን ጠቁመው፤ አንዳንድ ጊዜ በውጪ በሌላ ጊዜ ደግሞ በሀገር ውስጥ ጽንፈኛ ኃይሎች የመበተን አደጋ ማስተናገዱን ገልጸዋል፡፡
የለውጡ መንግሥት ወደ ስልጣን ከመጣ በላ የቀደሙት ትውልዶች ሠራዊትና የወቅቱ ጦር ኃይል ኢትዮጵያ ለመከለካል እየከፈለ ያለውን ዋጋ በእኩል መታየት እንዳለበት መወሰኑን አብራርተዋል፡፡
በዚህም ላለፉት ከመቶ ዓመታት በላይ አኩሪ ገድል ሲፈጽም የቆው መለዮ ለባሽ በቅብብሎሽ ያስረከበን ተግባር ነውና የጋራ ቀን ተደርጎ ከለውጡ ወዲህ በተከታታይ እየተከበረ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
የዘንድሮውን በዓል በግንባርና በደጀን ሀገራችንን፣ ህዝባችንን እና መንግሥታችን እያኮራ የሚገኘው ሠራዊት በያለበት በዓሉን እንደሚያከብር ገልጸዋል፡፡
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
በመልካም ፈቃዱ