የሀገር ውስጥ ዜና

በሁለቱ ውሃዎች የሚገኘውን የኢትዮጵያን ጥቅም ከማስከበር ውጭ አማራጭ የለንም – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

By sosina alemayehu

October 25, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) እኛ ኢትዮጵያውያን በዓባይ ወንዝ እና በቀይ ባሕር ላይ የሚገኘውን የኢትዮጵያን ጥቅም ከማስከበር ውጭ አማራጭ የለንም አሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ።

119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን “የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ነው።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ ማንሰራራት የህልውና አደጋ ያመጣብኛል በማለት ከ15ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲወጋን እና ሲያዋጋን የኖረ ጠላት በትግራይ፣ በአማራ እና ኦሮሞ ህልውና ውስጥ ተደብቆ እየወጋን ይገኛል ብለዋል። ‎ ‎ ‎የዓባይ ውሃ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ፀጋ ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ ቀይ ባሕር እኛ ኢትዮጵያውያን እንድንገለገልበት ፈጣሪ አበጃጅቶ የሰጠን ባሕር ነው ሲሉ ገልጸዋል። ‎ ኢትዮጵያውያን በሁለቱ ውሃዎች የሚገኘውን የኢትዮጵያን ጥቅም ከማስከበር ውጭ አማራጭ የለንም በማለት ገልጸው፤ ‎የመደመር መንግሥት የሁለቱን ውሃዎች ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የጎላ ሚና እንዳለውም አስገንዝበዋል።

ዓባይ እና ቀይ ባሕር ለሁሉም የሚበቁ ሀብት መሆናቸውን አንስተው፤ ነገር ግን የኢትዮጵያን የጋራ የውሃ ጥቅም ንቆ ብቻውን ለመጠቅለል የሚፈልግን ገብጋባ እየታገልን ነው ብለዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በእመቤት ሲሳይ