የሀገር ውስጥ ዜና

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በ119ኛው የመከላከያ ሰራዊት ቀን ሲከበር ባደረጉት ንግግር ያሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች:-

By sosina alemayehu

October 25, 2026

👉 ኢትዮጵያ ጥንታዊ ከሚባሉ ሀገረ መንግሥታት መካከል አንዷ ናት፤ ጠንካራ ተቋማት ከገነቡ ሀገራት ተርታም ትመደባለለች፤ 119 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያ ከገነባቻቸው ተቋማት አንጋፋ የሚባል ነው። ‎ ‎👉 ሠራዊቱ ለ119 ዓመታት ከውጭ ጠላት እና ከውስጥ ባንዳዎች ጋር እየተዋጋ ሀገር አቆይቷል። ‎ ‎ ‎👉 የሀገርን ሉዓላዊነት እና አንድነት መጠበቅ የመከላከያ ሠራዊት የተፈጥሮ ባህሪ ነው፤ መከላከያ የሀገረ መንግሥት ስርዓት እና የሀገር መኖር አለመኖርን የሚወስን የህልውና ምሰሶ ነው። ‎ ‎👉 መንግሥትን በመተው የፖለቲካ አንጃ እና ሸማቂ አካላት ተባባሪ መሆን አይችልም፤ ይህን አደረገ ማለት ከተፈጥሮ ባህሪው በመውጣት ሀገር እንድትፈርስ ፈቀደ ማለት ነው። ‎ ‎👉 በዲጂታል ዘመን መከላከያ ሠራዊትን እናፈርሳለን የሽግግር መንግሥት እናመጣለን የሚሉ ደፋር ባንዳዎች ተፈልፍለዋል። ‎ ‎👉 የሀገሪቱን ምሰሶ አፍርሰው ሀገር ለማፍረስ የከጀሉ ደፋር ባንዳዎች በታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች እየተነዱ እና እየተጫኑ ቋንቋቸው እየተደበላለቀ ገንጣይ እና ሽብርተኛ የባዕድ ተልዕኮ ተሸካሚ ፍጡራን ናቸው።

👉 በዚህ ዓመት መስከረም 13 ከግብፅ፣ ሱዳንና እና ኤርትራ የተቀናጀ ፅምዶ መላላክ የተጠናወተው ህገ ወጡ ህወሓት በሰሜን ወሎ፣ በዋግ እና በአፋር ግንባሮች ጦርነት ከፍቶ እራሱ በከፈተው ጦርነት እንዳልነበር ሆኗል። ‎ ‎👉 ከምፅዋ ወደብ የተላለፈላቸውን የአንድ መጠነኛ ሀገር የመከላከያ ትጥቅ ሊሆን የሚችል መሳሪያ ሰራዊታችን ተቆጣጥሯል። የጠላቶቻችን ዱለታ ሲያምራቸው ቀርቷል። ‎ ‎👉 መከላከያ ሠራዊት ተዳክሟል ትንሽ ከገፈተርነው ይፈርሳል ብለው በተነኮሱት ጊዜ ለመከላከያ ሠራዊት የተመኙትን መፈራረስ ፈራርሰው የትግራይን ህዝብ ንብረት ጭነው መንደፈራ ገብተዋል። 4ኛ ዙሩ በዘራችሁ አይድረስ ደርሶባቸዋል። ‎ ‎👉 ህገ ወጡ ህወሓት በዚህ ስምንት ዓመት ውስጥ 4 ትልልቅ ጦርነቶች ከፍቷል፤ ሁሉም ጦርነቶች በበቃኝ የተረቱ ናቸው ነገር ግን መረታቱን ላለመቀበል ስልታዊ ማፈግግፈግ አደረኩ እያለ ሽንፈቱን በፕሮፖጋንዳ ይሸፍናል። ‎ ‎👉 የትግራይ ህልውና፣ የኦሮሞ ህልውና፣ የአማራ ህልውና የሚለው መዝሙር ዋናውን ጠላት ለመደበቅ የተቀበረ መርዝ ነው፤ መርዙን ተሸክሞ የኢትዮጵያ ህልውና ላይ አደጋ የደቀነው ደግሞ የእኛ ባንዳ ነው።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በእመቤት ሲሳይ