የሀገር ውስጥ ዜና

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በ119ኛው የመከላከያ ሰራዊት ቀን ሲከበር ባደረጉት ንግግር ያሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች:-

By sosina alemayehu

October 25, 2026

👉 የኢትዮጵያ ማንሰራራት የህልውና አደጋ ያመጣብኛል በማለት ከ15ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲወጋን እና ሲያዋጋን የኖረ ጠላት በትግራይ፣ በአማራ እና ኦሮሞ ህልውና ውስጥ ተደብቆ እየወጋን ይገኛል። ‎ ‎ ‎👉 የዓባይ ውሃ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ፀጋ ነው፤ ቀይ ባሕር እኛ ኢትዮጵያውያን እንድንገለገልበት ፈጣሪ አበጃጅቶ የሰጠን ባሕር ነው። ‎ ‎👉 የመደመር መንግሥት እና መከላከያ በሁለቱ ውሃዎች የሚገኘውን የኢትዮጵያን ጥቅም ከማስከበር ውጭ አማራጭ የላቸውም።

👉 ዓባይ እና ቀይ ባሕር ለሁሉም የሚበቁ ናቸው፤ ነገር ግን የኢትዮጵያን የጋራ የውሃ ጥቅም ንቆ ብቻውን ለመጠቅለል የሚፈልግን ገብጋባ እየታገልን ነው። ‎ ‎👉 ልጆቻችን እኛን ክደው ለእነሱ እያገለገሉ ነው፤ እንደልማዳችን እንደ አያቶቻችን እየመከትናቸው እንገኛለን። ‎ ‎👉 ህገ ወጡ ህወሓት አራት እንቅፋት የመታው ፍጡር ነው፤ በዘመቻ ህግ ማስከበር፣ በዘመቻ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ ፕሪቶሪያው በወለደው ሶስተኛው ዘመቻ በሁሉም ተመትቶ ለአራተኛ ጊዜ ወደ ቆቦ፣ ሰቆጣ፣ ላሊበላ፣ ተኩለሽ እና አካባቢው መጥቶ ተመትቷል። ‎ ‎👉 አሁን ወደ ባልደረባው ሻዕቢያ የሄደው ህገ ወጡ ህወሓት አምስተኛ እድል እንዲኖረው አናደርገውም። ‎ ‎👉 የትግራይ እናቶች፣ ወጣቶች፣ ሽማግሌዎች፣ በህገ ወጡ ህወሓት የጦርነት አዙሪት የነበራቸውን ሁሉ አጥተዋል። ልጆቻቸውን በጉልበት እየተነጠቁ ወደ ጦርነት በመማገድ ትውልድ እንዲያጡ እና በሀዘን እንዲጎሳቆሉ አድርጓል።

👉 የትውልድ ቅብብሎሽ ተዛብቷል የነበራቸውን ጥሪት አሳጥቷቸዋል፤ እርዳታ ጠባቂ አድርጓቸዋል አሁን ከጎናቸው ቆመን እየተከላከልንላቸው እንገኛለን። ‎ ‎👉 ህገ ወጡ ህወሓት በሁለት ሳምንት ኢትዮጵያን እቀብራለሁ ብሎ ተነስቶ ሁለት ሳምንት ሳይሞላው ላይመለስ ተቀብሯል። ‎ ‎👉 ትግራይ ክልል አዳዲስ ሀሳቦች፣ አዳዲስ አመራሮች፣ ሰላም እና ልማት ትሻለች የግማሽ ምዕት ዓመት የግጭት አዙሪት የትግራይን ህዝብ ሁሉንም ነገር በልቶበታል። ‎ ‎👉 ጣቱ ሲቆስል ዝም ብሎ የሚያይ የለም እና እኛ ኢትዮጵያውያን ሁላችንም ልናግዛቸው ይገባል። ‎ ‎👉 ህገ ወጡ ህወሓት መከላከያን ሊያፈርስ ቋምጦ ነበር ተመትቷል፤ ሠራዊታችን ሰባት የፅምዶ ትብብር ቡድኖችን እና ሶስት የጀርባ የውጭ ሀይሎችን አሸንፏል፤ የቀጣናው አስተማማኝ ሀይል ሆኗል። ‎ ‎👉 ሊያፈርሱት የከጀሉትን ያፈርሳል እንጂ በመከላከያ ሠራዊት መቃብር ላይ የምትመሰርቱት የሽግግር መንግሥት የለም። ለሰላም እጅ ስጡ፣ ፖለቲካ እና ስልጣንን ከፈለጋችሁ ተደራጁና በሰላማዊ መንገድ ተወዳደሩ። ከባዕዳን ጋር ሆናችሁ በአቋራጭ ስልጣንን ለማግኘት መሞከር ከንቱ ምኞት ነው። ‎ ‎👉 በጫካ መንገድ ሞክራችሁ ሲያቅታችሁ መከላከያን ለማፍረስ አትንጠራሩ፤ መከላከያ የጠላትን ሴራ ያፈርሳል እንጂ አይፈርስም።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በእመቤት ሲሳይ