አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የ80 ዓመቱ ግራ ዘመም መሪ ሉዊስ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የብራዚል ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን አሸንፈዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቀኝ ዘመሙን ተቀናቃኛቸው እና የብራዚል የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጂየር ቦልሶናሮ ልጅ ሴናተር ላቪዮ ቦልሶናሮን በማሸነፍ ነው በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ የብራዚል የፕሬዚዳንት የሚሆኑበትን ድምፅ ያገኙት፡፡
በምርጫው ሉላ ዳ ሲልቫ 51 ነጥብ 79 በመቶ ድምፅ ሲያገኙ ተቀናቃኛቸው ላቪዮ ቦልሶናሮ 48 ነጥብ 21 በመቶ ድምፅ አግኝተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በፈረንጆቹ ጥቅምት 4 በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ተሸንፈው የነበሩ ቢሆንም፤ በሁለተኛው ዙር ምርጫ ግን ሳይገመቱ ማሸነፍ ችለዋል፡፡
በዚህም ሉላ ዳ ሲልቫ በብራዚል የዴሞክራሲ ታሪክ በአንደኛ ዙር ተሸናፊ ሆኖ በመጨረሻው ዙር ማሸነፍ የቻሉ የመጀመሪያው እጩ መሆን ችለዋል፡፡
ውጤቱ ይፋ ከሆነ በኋላ ፕሬዚዳንት ሉላ ድሉን “ታሪካዊ” ሲሉ የገለፁት ሲሆን፤ የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች በብራዚሊያ እና ሪዮ ዲ ጃኒዬሮ ከተሞች ደስታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡
ተፎካካሪያቸው ላቪዮ ቦልሶናሮ በበኩላቸው÷ ምርጫው ለሰዓታት የተራዘመበት ምክንያት ግልፅ አይደለም ያሉ ሲሆን፣ የምርጫ ውጤቱን እንደማይቀበሉት ለደጋፊዎቻቸው አሳውቀዋል፡፡
የብሪክሱ ቁልፍ ሰው ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ቀደም ሲል በፈረንጆቹ 2003 እስከ 2010 ሁለት ዙር እንዲሁም ከ2023 ጀምሮ ስልጣን ላይ ያሉበትን ጨምሮ በፕሬዚዳንትነት ሲመረጡ የአሁኑ ለአራተኛ ጊዜ ነው።
በሚኪያስ አየለ