የሀገር ውስጥ ዜና

ጸጋዎችን በመለየትና በማልማት ሕይወትን የማዳን ጉዞ

By betelhem girma

October 26, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ወንዞችን ማዳን ተፈጥሮን ከመጠበቅ ባለፈ፣ ሕይወትን የማዳን፣ የሕዝብን ጤና የማሻሻልና ለትውልድ የሚሻገር ዘላቂ የከተማ ልማት የመፍጠር ትልቅ ተልዕኮ ነው።

አዲስ አበባ ወንዞቿን እንደ ችግር ምንጭ ሳይሆን፣ እንደ ውድ የተፈጥሮ ፀጋና የልማት ዕድል በመለየት ወደ መመለስና ማደስ ጉዞ ተሰማርታለች።

ለዓመታት በብክለት፣ በቆሻሻ ክምችትና በተፈጥሮ ሥነ-ምህዳር መበላሸት የተጎዱትን ወንዞች በማጽዳት፣ ዳርቻዎቻቸውን በማልማት፣ አረንጓዴ ስፍራዎችን በመፍጠርና ለሕዝብ ጠቃሚ የመዝናኛና የእንቅስቃሴ ስፍራዎችን በማዘጋጀት የከተማዋን የተፈጥሮ ፀጋ ወደ ሕዝባዊ ትርፍ እየቀየረች ትገኛለች።

ይህ ልማት የወንዝ ዳርቻዎችን ውብ ከማድረግ በላይ ትርጉም አለው። የውኃ አካላትን ከብክለት ለመጠበቅ፣ የተፈጥሮ ሥነ-ምህዳርን ለማጠናከር፣ ለንጹሕ አየርና ለጤናማ አኗኗር የተሻለ ሁኔታ ለመፍጠር እንዲሁም ለከተማዋ ነዋሪዎች ደህንነትና የኑሮ ጥራት መሻሻል የሚያበረክተው ድርሻ ትልቅ ነው።

የተበከሉ ወንዞችን ወደ ጤናማ የተፈጥሮ ሀብትነት መመለስ የዛሬን ችግር ከመፍታት ባለፈ፣ የነገውን ትውልድ የሕይወት ጥራት የማረጋገጥ ኃላፊነት መሆኑን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአዲስ አበባ ወንዞች የማዳን ጉዞ በተፈጥሮ ውስጥ የተደበቁ ፀጋዎችን በመለየት፣ በልማት በማበልጸግና ለጋራ ጥቅም በማዋል ከተማን እንደገና የመፍጠር ተምሳሌት ነው።

ይህ የልማት ጥረት በመንግሥት ብቻ ሳይገደብ፣ የሁሉንም ዜጎች ተሳትፎና ኃላፊነት ይጠይቃል። ወንዞቻችንን ከብክለት መጠበቅ፣ ቆሻሻን በአግባቡ ማስወገድና የተመለሰውን የተፈጥሮ ሀብት በጋራ መንከባከብ የእያንዳንዳችን ድርሻ ነው።

ወንዞቻችንን ስናድን ተፈጥሮን እንጠብቃለን፤ ተፈጥሮን ስንጠብቅ ሕይወትን እናድናለን፤ ሕይወትን ስናድን ለትውልድ የሚተርፍ ዘላቂ ከተማ እንገነባለን!

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ