የሀገር ውስጥ ዜና

35 ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

By betelhem girma

October 26, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ጋር በመተባበር 35 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ አድርጓል።

ኤምባሲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው÷ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት አስከፊነትን በተመለከተ ለዜጎቻችን በተደጋጋሚ መረጃ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውሷል፡፡

ሆኖም ግን አሁንም መደበኛ ያልሆኑ የፍልሰት እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን የጠቆመው ኤምባሲው፤ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

ዜጎች ህጋዊ የፍልሰት አማራጮችን ብቻ በመከተል ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውን እና ማህበረሰቡን ከአካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት እንዲጠብቁ ኤምባሲው ጥሪ አቅርቧል፡፡