አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ለተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ሹመቶችን ሰጠ።
በዚህም መሰረት፦
- አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ- በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊና የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ
- አቶ ማሄ ቦዳ- የትምህርት ቢሮ ሃላፊ
- አቶ ተሾመ ታከለ- የኢንዱስትሪና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሃላፊ
- አቶ አክሊሉ አዱኛ- የውሃና መስኖ ልማት ቢሮ ሃላፊ
- አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል- የዴሞክራሲ ስርዐት ግንባታ ማሰተባበሪያ ማእከል ምክትል አስተባባሪ
- አቶ ይሁን አሰፋ- በዴሞክራሲ ስርዐት ግንባታ ማሰተባበሪያ ማእከል የህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ሚዳያ ዘርፍ ሃላፊ
- አቶ ንጉሴ አስረስ- የደቡብ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።