👉 የኢትዮጵያና የሩሲያ ወዳጅነት ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ በመከባበርና በአብሮነት አድጓል።
👉 እ.ኤ.አ. በ1896 የታላቁ የዓድዋ ጦርነት ወቅት የሩሲያ ቀይ መስቀል ቡድን ቁስለኞቻችንን ለማከም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ነበር።
👉 ቡድኑም አንድ የሕክምና መመሪያ መጽሐፍ ወደ አማርኛ ተርጉሟል። ያ ትንሽ የሚመስል ነገር ግን ትልቅ ትርጉም ያለው ተግባር ነበር፤ ዕውቀትን ወደ ፈውስ ለውጧል።
👉 ዓለም እየተለወጠች ነው፤ እዚህ ያዘጋጀነው የድርጊት መርሃ-ግብር ክርክሮችን ወደ ውጤት መቀየር አለበት።
👉 ብዙ አገሮች ለምርት እና ለሳይንስ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ፣ ሁላችንም ይበልጥ ጠንካራ እንሆናለን።
👉 ለኢትዮጵያ ይህ የሚጀምረው ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ነው። ነፃነት የመወሰን መብት ይሰጠናል።
👉 ጠንካራ አቅም ውሳኔዎችን ወደ ተግባር የምንለውጥበትን መንገድ ይሰጠናል።
👉በሦስት ዋና ዋና ዘርፎች ማለትም በምግብ፣ በኃይል እና በዕውቀት ላይ ኢንቨስት እያደረግን ነው።
👉 በምግብ ረገድ ቀዳሚ ዓላማችን ሕዝባችንን መመገብ እና ለዘላቂ ብልጽግና የሚሆን የግብርና ኢኮኖሚ መገንባት ነው።
👉ከሩሲያ ጋር የሚደረግ ትብብር በግብርና ማሽኖች እና የምንሰበስበውን ምርት በስፋት የሚያቀነባብሩ ኢንዱስትሪዎች አማካኝነት ይህንን ግብ ማሳካት ይቻላል።
👉 ኃይል ለዚህ ዓላማ ወሳኝ ነው። ከሩሲያ ጋር በመሆን ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) የደኅንነት ደረጃዎች ጋር የተጣጣመ የመጀመሪያውን የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት እየተንቀሳቀሰን ነው።
👉 የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በዋናነት በሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ላይ የተመሠረተውን የኃይል ማመንጫ ስብጥር ያብዛል።
👉 የኑክሌር ሳይንስ ከዚህ የላቀ ጠቀሜታ አለው፤ የምግብ ብክነትን መቀነስ እና ካንሰርን ለማከም ይረዳል።
👉 ይህ ትብብር ይህንን ተቋም ለማስተዳደር እና ለመቆጣጠር የሚያስችል የአገር ውስጥ ባለሙያዎችን ማፍራት አለበት።
👉 በዕውቀት ረገድ፣ አቅም ማለት አሁን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሠራሽ አስተውሎት) ማለት ነው።
👉 ሥርዓቶቹ የሚገነቡበት መንገድ የትኞቹ ቋንቋዎች እንደሚገለገሉ እና የማን ተሞክሮ እንደሚንጸባረቅ ይወስናል።
👉 አንድ አፍሪካዊ ተመራማሪ በሕዝባችን ቋንቋ መሣሪያዎችን መፍጠር መቻል አለበት፤ ተቋሞቻችንም እነዚህ መሣሪያዎች መረጃዎቻችንን እንዴት እንደሚጠቀሙበት መወሰን አለባቸው።
👉ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ «የመደመር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ» እያቋቋመች ትገኛለች።
👉 የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች እና ተቋማት በትምህርት እና በምርምር ከእኛ ጋር እንዲሠሩ እንጋብዛለን።
👉 ፈጠራ ወደ ምርት እና ንግድ መሸጋገር አለበት። አፍሪካ በአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) አማካኝነት ወደ አንድ ገበያነት እየገነባች ነው።
👉 የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የመድኃኒት እና የማሽነሪ ማምረቻ የጋራ ኢንቨስትመንቶችን በማቋቋም፣ ምርታቸውን ለአፍሪካ ገበያዎች ማቅረብ ይችላሉ።
👉በሀገሮቻችን መካከል ያሉ የክፍያ መንገዶች ንግድን ቀላል እና ርካሽ ማድረግ አለባቸው።
👉 ኢትዮጵያ፣ ሩሲያ በወዳጅነታችን ላይ ላላት ቁርጠኝነት ከፍ ያለ ቦታ ትሰጣለች። በበኩላችን ኃላፊነታችንን እንወጣለን።
👉አዲሱ የድርጊት መርሃ-ግብር ግልጽ ተግባራትን እና የጊዜ ሰሌዳዎችን እንዲያወጣ እናቀርባለን።
👉 ይህ ጉባኤ ወደ አፍሪካ ሲመጣ፣ የአፍሪካ ሕብረት መዲና የሆነችው አዲስ አበባ እሱን ለማስተናገድ ታላቅ ክብር ይሰማታል።
👉 ኢትዮጵያ ድርድርን የተከተሉ መፍትሔዎችን፣ አፍሪካ-መር ድርድሮችን፣ እና የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር ለሁሉም ሀገር በወጥነት ተግባራዊ እንዲሆን ትደግፋለች።
👉 የመደመር ፍልስፍናችን እያንዳንዱ አጋር የሚሰጠው ነገር እንዳለው ያሳያል።
👉 ከ130 ዓመታት በፊት የሩሲያ የሕክምና ዕውቀት ወደ አማርኛ ተተርጉሟል። ዘንድሮ ደግሞ «መደመር» መጽሐፍ ወደ ሩሲኛ ተተርጉሟል፤ ዕውቀት በሁለቱም አቅጣጫ እየተንቀሳቀሰ ነው።
👉ኢትዮጵያ ወደ ሞስኮ የመጣችው ለዚህ ዓይነቱ ሽርክና ነው።
በቴዎድሮስ ሳህለ