የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ6 ከተሞች 11 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ ጣቢያዎችን ሥራ አስጀመረ

By sosina alemayehu

October 31, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ6 ዋና ዋና ከተሞች 11 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ ጣቢያዎችን ባዛሬው ዕለት ሥራ አስጀምሯል።

የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌቱ ገረመው (ኢ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ፥ አዲስ የተገነቡት ማዕከላት እያንዳንዳቸው በአንድ ጊዜ ስድስት ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ናቸው።

ይህ አዲስ አቅም ቀደም ሲል የነበሩትን 3 የኃይል መሙያ ጣቢያዎች ወደ 14 ከፍ የሚያደርግ ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ ኃይል የመሙላት ሀገራዊ አቅምንም ከ54 ወደ 96 ያሳድገዋል ብለዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማስፋፋት በተያዘው ዕቅድ መሠረት የኃይል መሙያ ጣቢያ መሰረተ ልማቶችን መገንባትና ያልተቆራረጠ ኤሌክትሪክ ማቅረብ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው ፥ መሰረተ ልማቱ በቢሾፍቱ መገንባቱ ከተማዋ የቱሪዝም ማዕከል እንደመሆኗ መጠን አዲሶቹ ጣቢያዎች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ ናቸው ሲሉ አመልክተዋል።

በተካልኝ ኃይሉ