አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ ማንቼሰተር ዩናይትድን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ከ30 ጀምሮ በተደረገው ጨዋታ ሞርጋን ሮጄርስ በጨዋታ እና ኮል ፓልመር በፍፁም ቅጣት ምት የቼልሲን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
በጨዋታው አርጀንቲናዊው የማንቼሰተር ዩናይትድ ተከላካይ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በቀይ ካርድ ተሰናብቷል።
ውጤቱን ተከትሎም ቼልሲ ነጥቡን 16 በማድረስ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ማንቼሰትር ዩናይትድ በነበረበት 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡