ስፓርት

ማንቼስተር ሲቲ ሁለተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናገደ

By Mikias Ayele

October 31, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ማንቼስተር ሲቲ በብራይተን 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ያሲን አያሪ የብራይተንን ብቸኛ  ግብ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ብራይተን ነጥቡን ወደ 19 ከፍ ሲያደርግ ማንቼስተር ሲቲ የሊጉ መሪነቱን የሚያጠናክርበትን እድል አባክኗል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ጨዋታዎች ቦርንማውዝ ሊድስን 2 ለ 0፣ ኮቭንትሪ ሰንደርላንድን 3 ለ 1 እንዲሁም ብረንትፎርድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 ሲያሸንፉ ሀል ሲቲ እና ኢፕስዊች 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡