የሀገር ውስጥ ዜና

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ጂኦፓርክ በዩኔስኮ የዓለም ጂኦፓርኮች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ

By sosina alemayehu

November 02, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ጂኦፓርኮች ዝርዝር ውስጥ በማስመዝገብ የመጀመሪያዋን ታሪካዊ የጂኦፓርክ እውቅና አግኝታለች።

በዩኔስኮ የተመዘገበው ይህ ልዩ የተፈጥሮ ሀብት የኢትዮጵያን ድንቅ የጂኦሎጂ ቅርስ እና ስትራቴጂካዊ የቱሪዝም መስህቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ በጎላ ሁኔታ የሚያስተዋውቅ ከፍተኛ ብሔራዊ ስኬት ነው።

ይኸው ዓለም አቀፍ እውቅና በዘርፉ ለሚከናወኑ የልማትና የተፈጥሮ ቅርስ ጥበቃ ሥራዎች አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ሲሆን፣ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ቁጥር በመጨመር ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።