የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት የማዕድን ዘርፍ አጋርነት የጋራ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል – ኢንስቲትዩቱ

By sosina alemayehu

November 03, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የማዕድን ዘርፍ አጋርነት የጋራ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል አሉ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዱልዋሳ አብዱላሂ (ዶ/ር)።

ኢንስቲትዩቱ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር ከፍተኛ ጠቀሜታ ባላቸው ማዕድናት ላይ የፖሊሲ የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የአውሮፓ ህብረት ዲፕሎማቶች፣ የማዕድን ዘርፍ ተመራማሪዎች፣ የፖሊሲ አውጪዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

አብዱልዋሳ አብዱላሂ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት፤ የማዕድን ዘርፍ ለኢትዮጵያ ከአምስት አበይት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች መካከል አንዱ ነው።

ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

የማዕድን ዘርፍ ለኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መጠናከር ሚና እንዳለው ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን አቅም ለመጠቀም ትኩረት አድርጋ እየሰራች እንደምትገኝ ገልፀዋል።

ከአውሮፓ ህብረት ጋር የሚደረገውን የኢንቨስትመንት አጋርነትን ለማጎልበት የማዕድን ዘርፉን እንደ አንድ አማራጭ ለመጠቀም መታቀዱንም ጠቁመዋል።

በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚፈጠረው አጋርነት ዘርፈ ብዙ ጠቀሚታ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ዘርፉ ከቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ከልምድ ልውውጥ እንዲሁም ከሥራ እድል ፈጠራ አኳያ አበርክቶው ላቅ ያለ መሆኑ ተመላክቷል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በሔብሮን ዋልታው