አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ – 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ፋቲህ ቢሮል (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በቱርክዬ አንታሊያ እየተካሄደ በሚገኘው ከኮፕ – 31 ጉባኤ ጎን ለጎን ነው ከዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ፋቲህ ቢሮል (ዶ/ር) ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረጉት፡፡
ውይይቱ የሁለቱ ወገኖች ትኩረት ተመጣጣኝና ዘላቂ የኢነርጂ አቅርቦትን ማስፋፋት፣ በንጹህ ኢነርጂ ልማት ላይ ያለውን ትብብር ማጠናከር እና የአፍሪካን እየጨመረ የመጣውን የኢነርጂ ፍላጎትና የልማት ምኞት ለማሳካት የካፒታል ወጪን በመቀነስ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተመላክቷል።
በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች በ2027 በአዲስ አበባ በሚካሄደው ኮፕ – 32 ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ሰፊ የምክክር አቅጣጫዎችን መለዋወጣቸው ነው የተገለጸው።
በውይይቱም የኢነርጂ አቅርቦትን ማረጋገጥ፣ ዘላቂ ልማት እና የአየር ንብረት ርምጃዎች እርስ በእርስ የሚደጋገፉ የጋራ ቅድመ አጀንዳዎች መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡