አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ – 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከኔፓል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሺሲር ካናል ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ከሚገኘው የኮፕ – 31 ጉባኤ ጎን ለጎን ነው የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉት፡፡
በውይይታቸውም በአየር ንብረት ለውጥ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮችና በአዲስ አበባ ከሚካሄደው ኮፕ – 32 በፊት ትብብርን ስለማጠናከር መምከራቸው ተገልጿል።