አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ከህዳር 2 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ይከፈላል አሉ የክልሉ ባለአደራ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ ኃላፊ ኣታኽልቲ ሃ/ስላሰሴ።
ኃላፊው በሰጡት መግለጫ ፥ የደመወዝ ክፍያው እንዲጀምር በተደረገው ጥረት ውጤት በመገኘቱ ክፍያው ከነገ ጀምሮ እንደሚከናወን አረጋግጠዋል።
በክልሉ ከ140 ሺህ በላይ የሚሆኑ መንግሥት ሰራተኞች እንደሚገኙና ከነዚህ ውስጥም በአካል ተገኝቶ ሪፖርት ላደረገ የደመወዝ ክፍያው የሚጀምር መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ኣታኽልቲ የባለአደራ አስተዳደሩ በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች ተደራሽ በመሆን የተቋረጡ የመንግሥት ተቋማትንና አገልግሎቶችን ወደ ቀድሞ አሠራራቸው ለመመለስ እየሠራ እንደሚገኝ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች በደረሰው ውድመት ምክንያት የተቋረጡ አገልግሎቶችን መልሶ ለማስጀመር በሚደረገው ጥረት የመንግሥት ተቋማት ሠራተኞች ወደ ሥራ ቦታቸው በመመለስ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም አስረድተዋል።
በግዛቸው ግርማዬ