የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋና ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By tigist gizachew

November 11, 2026

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋና ፕሬዚዳንት ዱማ ጌዲዮን ቦኮ ጋር ከኮፕ31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ በውይይታችንም ሁለቱ ሀገሮች የተጋረጡባቸውን የጋራ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችና እየወሰድናቸው ያሉትን ምላሾች ጨምሮ በCOP32 ላይ ትብብራችንን ለማጠናከር፣ ጠንካራ የአፍሪካ አየር ንብረት አጀንዳን ወደፊት ማስቀጠል እንዲሁም በሌሎች ሰፊ የሁለትዮሽ ትብብር መስኮች ላይ መክረናል ነው ያሉት።

 

#ኢትዮጵያ #ኮፕ_32_ኢትዮጵያ #COP31 #COP32 #COP32ETHIOPIA #fanamediacorporation