አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤድ ሚሊባንድ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የወሰደቻቸውን ርምጃዎች በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የካርበን ልቀቶች መቀነስ አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።
ኤድ ሚሊባንድ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ኮፕ 32ትን በስኬት እንድታዘጋጅ ሀገራቸው ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ #ኮፕ_32_ኢትዮጵያ #fanamediacorporation