አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተርና ቺፍ ኖውሌጅ ኦፊሰር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በአንታሊያ ቱርክዬ እየተካሄደ ከሚገኘው የኮፕ31 ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደው ውይይት ላይ በኮፕ32 ዝግጅት ዙሪያ የሁለቱን ወገኖች ትብብር ስለማጠናከር መክረዋል፡፡
በተጨማሪም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (ኢ-ሞቢሊቲ)፣ በአየር ንብረት ፋይናንስ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ተግባራዊ አፈጻጸም እንዲሁም ከካርቦን ክሬዲት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።