ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Hailemaryam Tegegn

November 12, 2026

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ32 ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር በርናዴት አራክዊዬ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ በአንታሊያ ቱርክዬ እየተካሄደ ከሚገኘው የኮፕ31 ጉባኤ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት፤ ለኮፕ32 ዝግጅት ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በጋራ ቅድሚያ በተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በቅርበት ለመሥራትና ለሁሉም አካላት ትርጉም ያላቸው ውጤቶችን የሚያስገኝ የተሳካ ጉባኤ እንዲሆን ጥረቶቻቸውን ለማስተባበር ተስማምተዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ #ኮፕ_32_ኢትዮጵያ #fanamediacorporation