አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ጉዞ ለማፋጠን በርካታ መዋቅራዊ ለውጦችን እያደረገች ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ግንባር ቀደሙን ስፍራ የሚይዘው ፋይዳ (የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ) ነው፡፡
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለዲጂታል ሽግግር ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ ባለፉት ዓመታት ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንዲይዙ ሰፊ ስራ ተሰርቷል። በዚህም እስካሁን ድረስ ከ53 ሚሊየን የሚበልጡ ዜገች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ ሆነዋል።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ግብርናውን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ውስጥ የጎላ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ በገጠር አካባቢ የሚኖሩ አርሶና አርብቶ አደሮች መመዝገባቸው የግድ ነው። በመሆኑም የገጠሩ ማህበረሰብ እንዲመዘገብ በቅንጅት በተሰራው ስራ ውጤት መጥቷል።
ግብርና ሚኒስቴር ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራምና ከክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ዲጂታል መታወቂያን በገጠር ለማስፋት እና ዜጎችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር በተያዙ ግቦች መሰረት በሁሉም የገጠር አካባቢዎች የሚኖረው ማህበረሰብ የፋይዳ ተመዝጋቢ የሚሆንበት ዕድል ተፈጥሯል።
ዲጂታል መታወቂያን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ የግብርና እና ገጠር ትራንስፎርሜሽን ስኬታማ ለማድረግ አስፈላጊ ነው።
ፋይዳ መታወቂያ የግብርና ትራንስፎርሜሽንን፣ የገጠር ፋይናንስን የአርሶ አደሮች መረጃ አያያዝን፣ የመሬት አስተዳደር ስርዓትን ለማዘመን ከፍ ያለ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው።
የፋይናንስ ተደራሽነት፣ የግብርና ግብዓት፣ የአገልግሎት ተደራሽነትን፣ ለማፋጠን ዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ነው።
አርሶና አርብቶ አደሩን ከተረጂነት ለማላቀቅ እና አምራችነትን ለማበረታታት የተጀመሩ ስራዎችን ለማጠናከርም የራሱ የሆነ ሚና ስላለው ህብረተሰቡን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ዘመናዊ አርሶ አደር ለመፍጠር ወሳኝ የሆነውን የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፤ ለግብርና ዘርፍ እና ለገጠር ትራንስፎርሜሽን ስኬት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ዲጂታል መታወቂያን በተመለከተ ያለውን ግንዛቤን በማጠናከር አርሶና አርብቶ አደሩ በስፋት እንዲመዘገብ መትጋት ያስፈልጋል።
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ