ዓለምአቀፋዊ ዜና

አሜሪካ የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብን ጨምሮ በርካታ ወታደሮችን በመካከለኛው ምስራቅ አሰማራች

By Mikias Ayele

November 16, 2026

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ ግዙፍ የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብን ጨምሮ ተጨማሪ ወታደሮችን በመካለከለኛው ምስራቅ አሰማራች፡፡

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) እንዳስታወቀው፥ ሦስተኛውን የአውሮፕላን ተሸካሚ አውሮፕላን ጨምሮ ከ9 እስከ 10 ሺህ የሚደርሱ ተጨማሪ ወታደሮች ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተሰማርተዋል፡፡

በዚህም ዩኤስኤስ ቴዎዶር ሩዝቬልት የተሰኘው ግዙፍ የጦር መርከብ ከሳንዲያጎ ወደብ ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የጦር መርከቦች፣ ተዋጊ ጄቶች፣ የባህር ኃይል እግረኛ ወታደሮችና መርከበኞች እስከ ህዳር ወር መጨረሻ ድረስ ወደ አካባቢው እንደሚሰማሩ ነው የተገለጸው፡፡

ስምሪቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ የመካከለኛው ዘመን ምርጫ ማብቂያ በኋላ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ሊሰነዝሩ እንደሚችሉ መናገራቸውን ተከትሎ መጀመሩን ዎል ስትሬት ጆርናልን ጠቅሶ አረብ ኒውስ ዘግቧል፡፡

የሁለቱ ሀገራት የሰላም ድርድር በአሁኑ ወቅት የተቋረጠ ሲሆን፤ ቀደም ሲል ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር አዲስ ስምምነት መፈረም አስፈላጊ እንዳልሆነ በመግለጽ የዲፕሎማሲው በር መዘጋቱን መናገራቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

በፓኪስታን ተጀምሮ የነበረው ታሪካዊ የተባለለት የሰላም ድርድር ያለ ስምምነት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረትና ወታደራዊ ፍጥጫ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉ ነው የተገለጸው

በሚኪያስ አየለ