አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ በሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን አጉል ተልዕኮ ሰለባ የሆኑ ወጣቶች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር አወሉ አብዲ እና አቶ ጌታቸው ረዳ በመቐለ የተሃድሶ ሥልጠና ካጠናቀቁ የቀድሞ ታጣቂዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሥልጠናውን ካጠናቀቁት ከ16 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሠልጣኞች ከኮር አመራር እስከ ሻለቃ ማዕረግ የነበራቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አቶ ጌታቸው በዚህ ወቅት ÷ በትጥቅ ትግል የነበሩ ዜጎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በተሃድሶ ሥልጠና ማለፋቸው ለትግራይ ብቻ ሳይሆን ለመላ ኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ጉልህ ፋይዳ እንዳለው አውስተዋል፡፡
በቀጣይም መንግሥት የተሃድሶ ሥልጠና የመስጠት ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡
አሁንም በህገ ወጡ የህወሓት ቡድን አጉል ተልዕኮ ሰለባ እየሆኑ ያሉ ወጣቶች መንግሥት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ እንዲጠቀሙም ጥሪ አቅርበዋል።
በግዛቸው ግርማዬ