አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ከተሞች ለነዋሪዎች በቂና አስተማማኝ የመኖሪያ ቤቶች አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ ከማንኛውም ነገር የበለጠ ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ ነው፡፡
መዲናችን አዲስ አበባም በተለያዩ ስርዓቶች የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡
ባለፈው ዓመት መጀመሪያ ለይ ታላቁ ህዳሴ ግድብ በታላቅ ህዝባዊ ተሳትፎ እና የመንግሥት ቁርጠኝነት ግንባቀው ተጠናቅቆ በተመረቀበት ዕለት የሀገራችንን የቤት አቅርቦት ለመፍታት የሚያስችል ከወደ ጉባ አንድ ብስራት ተሰምቶ ነበር፡፡
በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ እና ወደ ብልጽግና ለማሸጋገር የሚያግዙ ሰባት ግዙፍ ስትራቴጂያዊ ፕሮጀክቶች እና ማሻሻያዎች ይፋ አድርገዋል። ከነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ ታዲያ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ አንዱ ነው፡፡
የመደመር መንግስት የቤት ልማት ግንባታ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል፣ የቤት እጦትን ለመቀነስ፣ ለቤተሰቦች የነገ ተስፋና የኢኮኖሚ ዋስትና ለመፍጠር ፕሮጀክቱን ይፋ አድርጓል።
ለዚህም በተቀናጀና በዘላቂነት የሚተገበር አገራዊ አቅጣጫ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል። ከሰሞኑ ታዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጉባ ብስራቶች ውስጥ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እየተገነቡ ያሉ ቤቶችን የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል፡፡
አርብ ህዳር 4 ቀን 2019 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቱሉ ዲምቱ የሚገኙ 33 እንዲሁም በአዲስ ከተማ ቅጠል ተራ የሚገኙ 9 ብሎኮች የግንባታ ሂደት ተጎብኝተዋል።
በመዲናዋ በ21 የቤት ልማት ሳይቶች 100 ሺህ ቤቶችን በስፋት እየገተነቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 50 ሺህ ቤቶች በከተማው በጀት፣ ቀሪዎቹ 50 ሺህ ደግሞ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት እንዲሁም በቤት ልማት ማኅበራት ግንባታቸው እየተካሄደ ነው።
በመርካቶ ቅጠል ተራ የተገነባው የበጎነት መንደር ዘጠኝ የመኖሪያ ቤት ሕንፃዎች የያዘ ሲሆን ከዚህ በፊት የነበረውን ጥሩ ያልሆነ ገጽታ እና የመኖሪያ ከባቢ በመቀየር ጤናማ እና ሳቢ የመኖሪያ ከባቢ ለመፍጠር የሚያስችል ነው፡፡
ቤቶቹ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ የሚቀይሩ፣ የቤተሰቦችን ተስፋ የሚያድሱና የማህበራዊ ፍትህን በተግባር የሚያረጋግጡ የመደመር መንግሥት ቁርጠኝነት ተጨባጭ ማሳያዎች ናቸው፡፡
የመደመር መንግሥት የዜጎችን የቤት አቅርቦት ፍላጎት ለማሟላት በመንግሥት፣ በማህበራትና በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት በማቀናጀት ግንባታዎችን እያፋጠነ ሲሆን ዘርፉን ችግር በከፍተኛ ደረጃ ለመቅረፍ የሚያስችል ነው፡፡
መንግሥት እንደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ፣ የጋዝ ፋብሪካ፣ የማዕድን ማቀውጫ፣ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሁሉ የቤት ግንባታ ፕሮጀክቶችንም በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለህዝብ ቃል የገባውን በተግባር እንደሚያሳይ አያጠራጥርም፡፡
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
በቴዎድሮስ ሳህለ